Wollo Meredaja Maheber Inc. (Meeting Place)
10315 Gilmoure Dr
Silver Spring , MD 20901
United States
myemail
Hello everyone, We finally got the full report from Dessie Committee members of Wollo Meredaja Maheber. They also send pictures and certificates of appreciation from those hospitals who recieved your donations. We will post them below for your review. If you have questions, please let us know.
The 7 Groups Joint committee!
ታህሳስ ፩፫፣ ፳፩፬ (December 22, 2021)
የሚመለከተው፥ ለደሴ ሪፈራል አጠቃላይ ሆስፒታል የበጎ አድራጎትን በተመለከተ ነው!
በኢትዮጲያ ሀገራችን አሸባሪዉ በጀመረዉ ጦርነት ምክንያት በብዛት የተፈናቀሉት በተለይ በአማራ እና በአፋር ተወላጆች ብዛቱ ቀን ከቀን እየተሥፋፋ እንደነበር ብሎም በአለም ላይ በሚሰራጨዉ የማሥ ሚድያ የእለት ከእለት አሣዛኝ ዜና መሆኑን ለማንኛዉም ሠዉ ግልጽ ነበር ነዉም። ይህንን ችግር በመረዳት በማንኛዉም እረገድ በተቻለን አቅምና መጠን መርዳት እንዳለብን በአሁኑ ሥአት በኢትዮጲያዉያን ልብና ህሊና ውስጥ በቁጭት እየተሰላሰለ ያለ ጉዳይ መሁኑን ለሁላችንም ግልጽ ነው። በዉስጥም በዉጭም ያላችሁ / ያለን ኢትዮጲያኖች በመረባረብ በአማራ እና በአፋር ላሉት የተጎዱ ወገኖቻችንን ለማቐቐም ዛሬም ነገም እርዳታቸሁን / እርዳታችንን ከምን ጊዜዉም በተጠናከረ መልኩ እንደምንቀጥል ተስፋችን ከፍ ያለ ነዉ።
ሆኖም በቅርቡ በጦርነቱ የተጎዱትንና የተፈናቀሉትን በተለይ በአፋርና በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን በደልና ግፍ ለማብራራት መሞከር ለቀባሪው ማርዳት ነው። በዚህም ምክንያት በደሴ ሪፈራል አጠቃላይ ሆስፒታል ላይ በደረሰው ዘረፋና ዉድመት ምክንያት ባስቸኮይ የሚያሰፈልጉትን የሆሰፒታል እቃወች ከሆስፒታሉ አሰተዳዳሪወች በሰጡን የሰም ዝርዝር መሠረት፣ በተፋጠነ መልኩ ገዝተን አስረክበናል። የእቃወቹ መግዣ የሚሖን፥ በመጠን $667,000.00 የኢትዮጲያ ብር አዉጥተን ደሴ በተቐቐመዉ የወሎ መረዳጃ ማህበር ጊዜአዊ ኮሚቴ በኩል እቃወቹን ገዝተዉ ለደሴ አጠቃላይ ሆስፒታል ሰባቱንም ድርጅቶች በመወከል እርዳታውን ያበረከቱልን መሆኑን በትሕትና እንገልጻለን።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ድርጅቶች በህብረት በመስራት እርዳታውን ያሰባሰቡት ናቸዉ።
፩) የኢትዮጲያዊያን ማህበረሰብ በአሪዞና፣
፪) የጎንደር ሕብረት፣
፫) አለም አቀፍ የአማራ ህብረት፣
፬) የአማራ ደሕንነትና ልማት ማህብር፣
፭) ልሳነ ግፉዓን ድርጅት፣
፮) የሸዋ ሁለገብ ማህበር፣
፯) የወሎ መረዳጃ ማህበር፣
ከላይ የተጠቀሱት አባላቶች ቤተስቦች እና በሌሎች የአሜሪካ ክፍለ ሐገራት የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያኖች እርዳታ በመለገስም ተሳትፈዋል፣ ምስጋናችንም ላቅ ያለ ነዉ።
ከዚህም በተጨማሪ ከላይ የተጠቀሱት ድርጅቶች፣ ከሦሥት ወር በፊት በመጠን ወደ $70,000.00 ዶላር (USD) የሚሆን የአማራ ክልል ለእርዳታ ማሰባሰቢያ በከፈተው የባንክ መዝገብ ቁጥር (አካውንት) ውስጥ በእርዳታ ማስገባታችንን ስንገልጽላችሁ በደስታ ሲሆን፣ በዚህ አጋጣሚ ለዚህም የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር የተሳተፉትን ወገኖች በሙሉ እናመሰግናለን።
ይሕንን በጎ አድራጎት ከጅምሩ እስከ አሁኑ ሥኬት ከጎናችን ሆነዉ ለረዱን ግለሰቦች እና ድርጅቶች ምሥጋናችን እጅጉን ከመጠን ያለፈ ነዉ።
በዋናነት ከዚሕ በታች የተጠቀሡትን ተባባሪ ግለሰቦች የወሎ መረዳጃ ማህበር ጊዜአዊ ኮሚቴዎቻችንን ሳናመሰግን አናልፍም።
፩) አቶ ተሥፋየ አሊ ዘገየ
፪) አቶ ፀጋየ ተሥፋማሪያም
፫) አቶ ጌታቸው ጨርቆሥ፥
በደሴ በተቐቐመዉ ጊዜአዊ ኮሚቴ አባሎች ሲሆኑ፥ ድጋፋቸው እንደባለፈው ዛሬም “ለወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚለው መርሆ መሠረት፥ በራሣቸዉ ወጭና ጊዜ በመጠቀም ከጎናችን ሆነው ላደረጉልን፥ ዓሁንም ለሚያደርጉልን ያላለሣለሠ ድጋፋቸው በሰባቱም ድርጅቶች ሰም ከልባችን እናመስግናለን።
በተጨማሪ፣ በደሴ ሪፈራል አጠቃላይ ሆስፒታል ለሚሰሩና ለሚያሰተዳድሩት ግለሰቦች በዚህ አሰቸጋሪና ፈታኝ ወቅት፣ ለህብረተሰቡ ለሚያደርጉት፣ ለሚሰጡት የህክምና አገልግሎት ከወድሁ ምስጋናችን ላቅ ያለ መሆኑን በትሕትና እንገልጻለን።
ኢትዮጲያ በልጆቹዋ ተከብራ ለዘለአለም ትኖራለች!
የሰባቱም ድርጅቶች ጊዜአዊ ገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴ (ከሰሜን አሜሪካ)
Copyright 2010 Wollo Meredaga Maheber . All rights reserved.
Wollo Meredaja Maheber Inc. (Meeting Place)
10315 Gilmoure Dr
Silver Spring , MD 20901
United States
myemail