Wollo Meredaja Maheber Inc. (Meeting Place)
10315 Gilmoure Dr
Silver Spring , MD 20901
United States
myemail
June 14, 2021
1. ከ2010 ዓ.ም በኾአላ በሀገራችን ኢትዮጵያ ታይቶ የማይታወቅ መልኩ ጭካኔ የተሞላበት ብሄር እና ሀይማኖት ተኮር በማስመስል ብዙ ጭፍጨፉወች ተካሂደዋል:: ይህ ብሄር ተኮር ግድያ በሌሎችም ብሄር ብሄረስቦች ላይም እንዳለ ሁኖ በተለይ በአማራ ብሄርና ቋንቋውን ተናጋሪዎች ላይ የጅምላ ግድያ፣ ሀብት ንብረታቸውን ማቃጠል፣ መዝረፍ እና በማፈናቀል ከኦሮሚያ፣ ከመተክል፣ ከአፋር፣ከከሚሴ፣ከአጣዬ የአማራ ህዝብ ሀብት ንብረታቸውን በመጣል ህይወታቸውን ለማትረፍ በደብብ ወሎ በ6 ጣቢያዎች ከ16,000 በላይ ተፈናቃዬች በአሁኑ ሰአት ተጠልለዉ ይገኛሉ::
2. ተፈናቃዬቹ ከህዝብ እና ከመንግስት ከሚደረግላቸው ውስን ድጋፍ ውጭ ምንም አይነት አማራጭ ሳይገኝ በከባድ ስቃይ ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ:: ይህን ችግር በማህበራዊ ድህረ ገፅ እና በሚዲያ ተለቆ ያየን በስሜን አሜሪካ በዲሲ ፣ቨርጂኒያ እና ሜሪላንድ አካባቢ የምንገኝ የወሎ መረዳጃ ማህበር አባላትና እንዲሁም አባል ያልሆኑ በተለያዩ እስቴት የሚኖሩ በጐ አድራጊ ኢትዮጵያኖች እኔስ ለወገኔ በማለት በወሎ መረዳጃ ማህበር ስር ገንዘቡን አስባስበን በላክነው መሰረት ከ$711,000 ብር በላይ እርዳታ ልከን:* 471 ብርድልብስ ፣* 300 ፍራሺ ፣* 6 ጥቅል የላስቲክ የወለል ምንጣፍ በመግዛት ለተረጀው ወገናችን በ6 ጣቢያ:
* በኩታበር ፣* በሀይቅ ፣* በጃሪ ፣* በአርጎባ ፣ * በደጋን፣ * በመካነስላም ለተጠለሉ ተፈናቃይ ወገኖቻችን እርዳታው ደሴ ባሉት የጊዜአዊ የኮሚቴ አባላቶች ጥረት ተከፋፍሏል። ሆኖም ግን ወገኖቻችን ይህች መጠኖአ ብታንስም ግን እኔም ወገን አለኝ ለካ ብለው ውስጣዊ ደስታቸውን አካፍለውናል::
3. እነዚህ ተፈናቃዬች የደረስባቸው መከራ እና ስቃይ እንዲሁም ስቆቃ ለመስማት የሚስቀጥጥ ለማየት ልብ የሚነካ አፀያፊ ተግባር ቢሆንም አሁንም የተፈናቃዬቹም ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ በደብብ ወሎ ከ6 ጣቢያውዎች ወደ 10 ጣቢያዎች ከፍ ብሏል ::
ከወለጋ የተፈናቀሉ ትውልደ ዓማራወች፦
4. እንዲሁም በስሜን ወሎ ውስጥም የተፈናቃዬቹ ቁጥር እየጨመረ ነው:: የባሰ ችግር ላይ እንዳይወድቁ አሁንም የወገን ድጋፍ የሚፈልጉ ናቸው ። ለጊዜው የተዋጣውን ገንዘብ ከላክን በኾላ: ጥቂት ወገኖች ኢትዪጲያኖች የለገሱልን ገንዘብ ወደ $1650 ብር ደርሶል:: እና አሁንም በተቻለን መጠን በሰሜን ወሎ ተፈናቅለው ያሉትን ወገኖች ካለችን ገንዘብ ላይ ጨምረን; ለምነን የተቻለንን እርዳታችን / እርዳታችሁን እንድናደርግላቸው በፈጠራችሁ/ በምታምኑት አምልክ እንማጸናለን::
ከዚህ ቀጥሎ ለዚህ የነፍስ አድን እርብርቦሽ በአጭር ጊዜ ጥሪያችንን ሰምታችሁ ለረዳችሁ ውድ ኢትዮጲያኖች በሙሉ: ምንም ቢሆን ችግሩም የናንተም ቢሆንም ቅሉ ምስጋናችን ከመጠን ያለፈ ነው:: ያው እንደምታውቁት ያገራችን ችግር ተቀርፎ አያልቅም ግን በጣም አጣዳፊ ጉዳይ ላይ በተለይ እረሀብ ጊዜ አይሰጥምና በተቻለን መጠን እጃችንን በወገኖአችን ላይ እንዳናጥፍ በጥሞና እንለምናለን:: በወጣ ይተካላችሁ!
በመጨረሻም ቪድዮውም ሆነ ፎቶወች በቴክንክ ምክንያት ስለዘገየብን የወሎ መረዳጃ ማህበር እና የደሴው ጊዜአዊ ኮሚቴወች ይቅርታ እንጠይቃለን::
ያም ሆነ ይህ: በተለይ የደሴውን ጊዜአዊ ኮሚቴወች ያው ቪድዮው ላይ ስማቸው እንደተዘረዘረው ምስጋናችን ላቅ ያለ መሆኑን እና ለወደፊትም በምንሰራቸው ስራ እንደሚተባበሩን ተስፋ አለን::
ልዩ ምስጋና:ገንዘባቸውንና ጊዜአቸውን ሰውተው ስልክ ቀንም ማታም እየደወሉ ከጅምሩ እስከመጨረሻው ሲሰሩ ለነበሩት የጊዜአዊ ኮሚቴ አባሎች መካከል: 1) አርቲስት ጸሀይ ካሳን ሞቅ ያለ ምስጋና ከልባችን እናቀርባለን::2) የወሎ መረዳጃ ማህበር ሊቀምንበር አቶ ተስፋየ ገላነውንም ሞቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን::
ከወሎ መረዳጃ ማህበር ጊዜአዊ ኮሚቴ!!
የስራችሁን ውጤት ከዚህ በታች በተለጠፈው ቪድዮ እና ፎቶወች ይመልከቱ::
ኢትዮጲያን እና ህዝቦን የምናምነው ፈጣሪ በሰላም እንዲጠብቅልን ምኞታችን ነው!!
Encourage People you know to help the desplaced Ethiopians specially the Amharas.
Don't hesitate to contact us with your questions or comments. Please see our Contact Us page for complete contact information.
Copyright 2010 Wollo Meredaga Maheber . All rights reserved.
Wollo Meredaja Maheber Inc. (Meeting Place)
10315 Gilmoure Dr
Silver Spring , MD 20901
United States
myemail